Your browser does not support HTML5 video.
ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት
Sorry, the time is up.
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ መሠረት ነጻ ፌዴራላዊ መንግሥት አካል ሆኖ የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ የሚሠራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው፡፡ (የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55/14 እና አዋጅ ቁጥር 210/1992 በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው)
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በኢሰመኮ የ2016 በጀት ዓመት የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ በመሆን ከተለዩት ጉዳዮች መካከል በሴቶች ሕይወት እና በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብት ዙሪያ ያተኩራል።
ኢሰመኮ የመንግሥት ተቋም ቢሆንም በተቋማዊ ነጻነት መርሕ የሚሠራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው፡፡ ነጻና ገለልተኛ የሆነ አመራርን፣ ባለሙያ የሆኑ ሠራተኞችን እና የፋይናንስ አጠቃቀም ነጻነትን በመጠቀም ኮሚሽኑ ከመንግሥት አስፈጻሚ አካላት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሌሎች አካላት በኩል ያለውን ነጻነት ያስጠብቃል፡፡
የአመራርና የሠራተኛ ጥንቅራችን ብዝኃነት ያለውና አካታች እንዲሆን እንጥራለን፡፡ እንዲሁም በተልዕኳችንና በተግባር ኃላፊነታችን አድልዎንና መገለልን ለማስወገድ እንሠራለን፡፡ በዚህም የኢትዮጵያን ሕዝብ ብዝኃነትን እናንጸባርቃለን፡፡
የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከደረሰባቸውና ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጋላጭ ከሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጎን በመቆም መብታቸውን እንዲጠይቁና እንዲጠቀሙ እናበቃለን፤ ድጋፍ እናደርጋለን፡፡
ሥራዎቻችንን እና የምናቀርባቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች (ምክረ ሐሳቦቻችን) በእውነታና ማስረጃ ላይ እንዲመሠረቱ አስፈላጊውን ጥረት እናደርጋለን፡፡ የሙያ ሥነ ምግባሮችን፣ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን በከፍተኛ ደረጃ እንጠብቃለን፡፡
ሁሉም ሰው ለራሱ እና ለቤተሰቡ በቂ፣ ደኅንነቱና ደረጃው የተጠበቀ፣ በአካል ተደራሽ የሆነ እና ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት አለው
ማንኛዋም ሴት ለሕይወቷ እና ለአካል ደኅንነቷ ክብር የማግኘት መብት አላት፡፡ ሁሉም ዐይነት ብዝበዛ፣ ጨካኝ፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት እና አያያዝ የተከለከለ ነው
This site was created with the Nicepage