በመርኃ ግብሩ የሚቀርቡ ፎቶግራፎች፣ ሥዕል፣ አጫጭር ፊልሞች እና አጫጭር የሥነ ጽሑፍ ውድድር : በ2017 ዓ.ም. በታኅሣሥ 01 ቀን የሚውለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን (December 10) በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ4ኛው ዙር የፊልም ፌስቲቫል ለዕይታ የሚቀርቡ የፎቶግራፍ፣ የአጫጭር ቪዲዮዎች እና የአጫጭር ሥነ ጽሑፍ ውድድሮች ያዘጋጀ ሲሆን፣ በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን ይመልከቱ
የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ የተዘጋጀው አራተኛው የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ለዕይታ ከሚቀርቡ የፊልም ውጤቶች በተጨማሪ የተለያዩ የኪነጥበብ ሥራዎች ማለትም የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፣ ሥዕል እና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ይገኙበታል። በዚህ ፌስቲቫል በተለያዩ ከተሞች በሚዘጋጁ መርኃ ግብሮች ላይ ለዕይታ የሚቀርቡ ፎቶግራፎች፣ የሥዕል ሥራዎችና ሥነ ጽሑፎች የተለያዩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በሚሳተፉበት ውድድር ከዝግጅቱ ቀን አስቀድሞ የሚመረጡ ናቸው።
ጭብጥ፡- የሴቶች ሕይወት
ይህ የውድድር ዘርፍ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ተሳታፊዎች በሴቶች ሕይወት የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቱ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ ሥራዎችን የሚያቀርቡበት ነው።
ከሰብአዊ መብቶች እና ከዘንድሮ ጭብጦች ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ፊልሞች ይታያሉ
በሴቶች ሕይወት ዙርያ በተሠሩ የኪነጥበብ ሥራዎች መካከል በሚደረግ ውድድር የተለዩ አሸናፊዎች ይሸለማሉ
በባለሙያዎች እና በታዳሚዎች መካከል ውይይት ይካሄዳል
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብቶች ባለሙያዎች እንዲገናኙ የሚያስችል መድረክ
ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ፍኖተ ቀበሌ፣ አረጋውያን ሕንጻ፣ 3ተኛ ፎቅ፣ ባሕር ዳር፣ ኢትዮጵያ
This site was created with the Nicepage