Jimma

በመርኃ ግብሩ የሚቀርቡ ፎቶግራፎችሥዕል፣ አጫጭር ፊልሞች እና አጫጭር የሥነ ጽሑፍ ውድድር : በ2017 ዓ.ም. ታኅሣሥ 01 ቀን የሚውለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን (December 10) በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ4ኛው ዙር የፊልም ፌስቲቫል ለዕይታ የሚቀርቡ የፎቶግራፍ የአጫጭር ቪዲዮዎች እና የአጫጭር ሥነ ጽሑፍ ውድድሮች ያዘጋጀ ሲሆን፣ በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን ይመልከቱ 




ጅማ

አራተኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በጅማ

የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ የተዘጋጀው አራተኛው የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ለዕይታ ከሚቀርቡ የፊልም ውጤቶች በተጨማሪ የተለያዩ የኪነጥበብ ሥራዎች ማለትም የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፣ ሥዕል እና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ይገኙበታል። በዚህ ፌስቲቫል በተለያዩ ከተሞች በሚዘጋጁ መርኃ ግብሮች ላይ ለዕይታ የሚቀርቡ ፎቶግራፎች፣ የሥዕል ሥራዎችና ሥነ ጽሑፎች የተለያዩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በሚሳተፉበት ውድድር ከዝግጅቱ ቀን አስቀድሞ የሚመረጡ ናቸው። 

ውድድሮች

ጭብጥ፡- በቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት

ማብራሪያ

ይህ የውድድር ዘርፍ ምግብና ውሃ  በማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ተሳታፊዎች በቂ ስለሆነ ምግብና ውሃ የማግኘት መብት የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቱ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ ምስሎችን (ፎቶግራፎችን) የሚያቀርቡበት ነው። 

በቂ የሆነ ምግብ እና ውሃ ማለት ምን ማለት ነው? ምግብ እና ውሃ የሌለው ሰው አኗኗር ምን ይመስላል? ምግብና ውሃ የማግኘት መብት ለሴቶች እና ለወንዶች አንድ ዐይነት ትርጉም አለው? የአካል ጉዳተኞች ምግብና ውሃ የማግኘት መብት ምን ይመስላል? 

ይህ የፎቶግራፍ ውድድር ዘርፍ እነዚህን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በምስል ለመግለጽ እና ለማሰላሰል የሚጋብዝ ነው። በዚህ የውድድር ዘርፍ በጀማሪም ይሁን ልምድ ባለው ባለሙያ ለሚቀርቡ የኪነጥበብ ሥራዎች የመወዳደሪያ መስፈርቶች ተመሳሳይ ናቸው። 

  • ለውድድር የሚቀርበው ፎቶግራፍ ለዘርፉ ከተመደበው ጭብጥ/ርዕሰ ጉዳይ ጋር (በቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት) ተያያዥነት ያለው ሊሆን ይገባል።

  • በዚህ ዘርፍ የሚቀርቡ የፎቶግራፍ/የኪነ ጥበብ ሥራዎች ከመስከረም ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ የተነሱ/የተወሰዱ ሊሆን ይገባል።

  • ለዚህ ውድድር የሚቀርቡ ሥራዎች ከ1 ሜጋ ባይት ያላነሱ እና ከ5 ሜጋ ባይት የማይበልጡ ሊሆን ይገባል። በ JPEG ሴቭ የተደረጉ እና በተቻለ መጠን ለኅትመት አመቺ በሆነ ከፍተኛ የጥራት (ሪዞሉሽን) ደረጃ ሊሆኑ ይገባል።

  • ለፎቶግራፍ ሥራ ከሚያስፈልገው የአርትዖት (editing) ሥራ በተጨማሪ፣ መጠነኛ በሆነ መልኩ ፎቶግራፉን ለማሳመር የሚደረጉ (digital manipulations) ሥራዎች ተቀባይነት አላቸው። ሆኖም እነኚህ ለውጦች ምን እንደሆኑ እና ለምን ዓላማ እንደተሠሩ በተሳትፎ ቅጹ ላይ በግልጽ ሊመላከት ይገባል። የውድድሩ አዘጋጆች ይህንን በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለተሳታፊው ሊያቀርቡ ይችላሉ። እንዲሁም ተጨማሪ ሥራዎች ያልተሠራበትን (ኦሪጂናል) ፎቶግራፍ እንዲላክ ሊጠይቁ ይችላሉ።

  • ተሳታፊው የሚጠቀመው ካሜራ ቢያንስ 3000 ፒክሰል (ወደ ጎን) እና 300 DPI/PPI setting ሊሆን ይገባል። በሞባይል/ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚነሱ ፎቶግራፎች ይህንን መስፈርት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ባይሆንም፣ ለውድድር ተቀባይነት የሚኖራቸው ከፍተኛ ጥራት (high resolution) ያላቸው እና ከተመደበው ጭብጥ/ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ከሆነ ብቻ ነው።

  • በተለይ በአንድ ሰው ላይ የሚያተኩሩ ፎቶግራፎች ከሆኑ የዛን ሰው ሙሉ ፈቃድ ማግኘት፣ ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ደግሞ በሕግ ሙሉ መብት ያለውን ወይም የአሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ማግኘቶትን ያረጋግጡ።

  • Collage ወይም በአንድ ፍሬም በርካታ ምስሎችን የያዘ ፎቶግራፍ በውድድሩ አይካተትም። ለውድድር በሚቀርበው ፎቶግራፍ ላይ ፊርማ፣ watermark፣ overlay እና የመሳሰሉትን ምልክቶች ወይም ጽሑፎች መጨመር አይገባም።

መርኃ ግብር

ፊልም ማሣየት

ከሰብአዊ መብቶች እና ከዘንድሮ ጭብጦች ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ፊልሞች ይታያሉ

የሽልማት ፕሮግራም

በበቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት ዙርያ በተሠሩ የኪነጥበብ ሥራዎች መካከል በሚደረግ ውድድር የተለዩ አሸናፊዎች ይሸለማሉ

የፓናል ውይይቶች

በባለሙያዎች እና በታዳሚዎች መካከል ውይይት ይካሄዳል

የመተዋወቂያ መድረክ

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብቶች ባለሙያዎች እንዲገናኙ የሚያስችል መድረክ

Flickr Gallery

ምስሎች

ያግኙን

አድራሻ

አዌቱ መንደራ ቀበሌ፣ ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጠገብ አቡነ እስጢፋኖስ ሕንጻ ላይ፣ ጅማ፣ ኢትዮጵያ 

የሥራ ሰዓት