Samara

በመርኃ ግብሩ የሚቀርቡ ፎቶግራፎችሥዕል፣ አጫጭር ፊልሞች እና አጫጭር የሥነ ጽሑፍ ውድድር : በ2017 ዓ.ም. ታኅሣሥ 01 ቀን የሚውለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ቀን (December 10) በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በ4ኛው ዙር የፊልም ፌስቲቫል ለዕይታ የሚቀርቡ የፎቶግራፍ የአጫጭር ቪዲዮዎች እና የአጫጭር ሥነ ጽሑፍ ውድድሮች ያዘጋጀ ሲሆን፣ በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን ይመልከቱ 




የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀንን ለማሰብ የተዘጋጀው አራተኛው የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ዓመታዊ ፊልም ፌስቲቫል በኅዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ለዕይታ ከሚቀርቡ የፊልም ውጤቶች በተጨማሪ የተለያዩ የኪነጥበብ ሥራዎች ማለትም የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን፣ ሥዕል እና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ይገኙበታል። በዚህ ፌስቲቫል በተለያዩ ከተሞች በሚዘጋጁ መርኃ ግብሮች ላይ ለዕይታ የሚቀርቡ ፎቶግራፎች፣ የሥዕል ሥራዎችና ሥነ ጽሑፎች የተለያዩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በሚሳተፉበት ውድድር ከዝግጅቱ ቀን አስቀድሞ የሚመረጡ ናቸው። 

ውድድሮች

ጭብጥ፡- በቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት 

ማብራሪያ

ይህ የውድድር ዘርፍ በበቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን ተሳታፊዎች በበቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቱ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ ምስሎችን (ፎቶግራፎችን) የሚያቀርቡበት ነው። 

በዚህ የውድድር ዘርፍ በጀማሪም ይሁን ልምድ ባለው ባለሙያ ለሚቀርቡ የኪነ ጥበብ ሥራዎች የመወዳደሪያ መስፈርቶች ተመሳሳይ ናቸው።  

  • ለውድድር የሚቀርበው ሥዕል ለዘርፉ ከተመደበው ጭብጥ/ ርዕሰ ጉዳይ ጋር (በቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት) ተያያዥነት ያለው ሊሆን ይገባል። 
  • በዚህ ዘርፍ የሚቀርቡ የሥዕል ሥራዎች ከመስከረም ወር 2016 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ የተሠሩ ሊሆኑ ይገባል።
  • ለዚህ ውድድር የሚቀርቡ የኪነጥበብ ሥራዎች ከ1 ሜጋ ባይት ያላነሱ እና ከ5 ሜጋ ባይት ያልበለጡ ሊሆኑ ይገባል። 
  • በተለይ በአንድ ሰው ላይ የሚያተኩሩ ሥዕሎች ከሆኑ የዛን ሰው ሙሉ ፈቃድ ማግኘት፣ ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ደግሞ በሕግ ሙሉ መብት ያለውን ወይም የአሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ማግኘትዎን ያረጋግጡ። 
  • የተፈቀዱ የሥዕል ዐይነቶች፡-
    • ማንኛውም 2D  ሥዕል ተቀባይነት ያለው ሲሆን፣ በእርሳስ፣ በቻርኮል፣ በየውሃ ወይም የዘይት ቀለሞች፣ ባለቀለም እርሳሶች፣ አክሬሊክስ ቀለሞች እንዲሁም በወረቀት ወይም ዲጂታል ሚዲያዎች በተጨማሪ በሸራ ላይ የተሠሩ ሥዕሎች ተቀባይነት አላቸው።  
  • ገደቦች፡-
    • 3D የተሠሩ ወይም ቁሳቁሶችን የሚያካትቱ ቅርጻ ቅርጾች ወይም ድብልቅ የሆኑ ሥራዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። 
    • ተሳታፊዎች ከኪነጥበብ አቅርቦቶች ጋር የተያያዙ ወጪዎችን መሸፈን የራሳቸው ኃላፊነት ሲሆን እንደ ሸራ፣ ቀለም፣ ብሩሽ፣ ወይም ሌላ ማንኛውንም ሥራቸውን ለመፍጠር ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሳቁሶች ማካካሻ ወይም የቅድሚያ ክፍያ አይሰጥም። 
  • የመጠን መስፈርቶች፡
    • በአካል ለሚቀርቡ ሥራዎች፡-
      • በወረቀት የሚቀርቡ ሥዕሎች፣ የሚፈቀዱት መጠኖች A3 ወይም A4 ናቸው። 
      • ለሸራ ሥዕሎች ከፍተኛው መጠን 50 x 70 ሴ.ሜ ነው። 
    • በዲጂታል ለሚላኩ ሥራዎች፡-
      • በከፍተኛ ጥራት ስካን የተደርጉ ወይም በጥራት ፎቶግራፍ የተነሱ መሆን አለባቸው። ምስሎቹ በበቂ ብርሃን የተነሱ፣ ግልጽ እና ከጥላዎች እና ሌሎች የምስሉን ጥራት ከሚያጓድሉ ነገሮች የፀዱ መሆን አለባቸው። 

መርኃ ግብር

የመክፈቻ ፕሮግራም

ከሰብአዊ መብቶች እና ከዘንድሮ ጭብጦች ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ፊልሞች ይታያሉ

የሽልማት ፕሮግራም

በበቂ ምግብ እና ውሃ የማግኘት መብት ዙርያ በተሠሩ የኪነጥበብ ሥራዎች መካከል በሚደረግ ውድድር የተለዩ አሸናፊዎች ይሸለማሉ

የፓናል ውይይቶች

በባለሙያዎች እና በታዳሚዎች መካከል ውይይት ይካሄዳል

የመተዋወቂያ መድረክ

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብቶች ባለሙያዎች እንዲገናኙ የሚያስችል መድረክ

Flickr Gallery

ምስሎች

ያግኙን

አድራሻ

በሰመራ ሎጊያ መንገድ፣ ወደ ሰመራ አየር መንገድ መገንጠያ በአዲሱ ሕንጻ ላይ፣ ሰመራ፣ ኢትዮጵያ 

የሥራ ሰዓት