2025 Competition Now Open!

የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር

የዘንድሮ ውድድር ጭብጥ፡- የነጻነት መብት እና የትምህርት መብት

ለውድድሩ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን የመላክ ሂደት

ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. (እኩለ ለሊት ወይም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት) ድረስ ለውድድር የሚቀርበውን የጥበብ ሥራ እንዲሁም የተሞላ እና የተፈረመበት የተሳትፎ ቅጽ በማያያዝ ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ መላክ ይችላሉ።

በኢሜል filmfest@ehrc.org 
በቴሌግራምTelegram: Contact @ethiohrc
በሚከተሉት አድራሻዎች በሚገኙት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢሮዎች በአካል በመገኘት 
የጥበብ ሥራውን በሲዲ (CD) ወይም በፍላሽ ዲስክ (USB) በፖስታ የታሸገ 
አዲስ አበባ ሰንሻይን ታወር ቁጥር 5፣ መስቀል አደባባይ አለፍ ብሎ ቦሌ መንገድ፣ ሀያት ሬጀንሲ ሆቴል አጠገብ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር 
ዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ፍኖተ ቀበሌ፣ አረጋውያን ሕንጻ 3ኛ ፎቅ፣ ባሕር ዳር፣ ኢትዮጵያ 
+25158 226 24 71 
ጋምቤላ ከሞቢል ፊት ለፊት/ከዊቡር የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎን፣ ጋምቤላ፣ ኢትዮጵያ 
+25147 551 13 76/ +25147 551 22 06 
ሃዋሳ መናኽሪያ – ሚለንየም መንገድ፣ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ፣ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ 
ሃዋሳ፣ ኢትዮጵያ 
+25146 220 59 74 
ጅግጅጋ 
ከቀበሌ 10 ጽሕፈት ቤት አጠገብ፣ ከፋራህ መጎል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት፣ ጅግጅጋ፣ ኢትዮጵያ 
+25125 278 42 14/ +25125 278 16 84 
ጅማ አዌቱ መንደራ ቀበሌ፣ ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጠገብ አቡነ እስጢፋኖስ ሕንጻ ላይ፣ ጅማ፣ ኢትዮጵያ 
+25147 111 40 43/ +25147 111 64 40 
አሶሳወረዳ 1 – መብራት ኃይል ቢሮ ፊት ለፊት፣ ወደ አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያቋርጠው መንገድ፣ አሶሳ፣ ኢትዮጵያ
+25157 775 08 50/ +25157 775 00 55/ +25157 775 06 90
ሰመራ 
በሰመራ ሎጊያ መንገድ፣ ወደ ሰመራ አየር መንገድ መገንጠያ አዲሱ ሕንጻ ላይ፣ ሰመራ፣ ኢትዮጵያ 

ከዚህ በላይ በተገለጹት የኢሰመኮ ጽሕፈት ቤቶች በአካል ተገኝተው የኪነጥበብ ሥራቸውን ለሚያቀርቡ ተሳታፊዎች የሚሞላው የተሳትፎ ቅጽ እና ፖስታ ይዘጋጃል። 

በኢሰመኮ ድረገጽ አልያም በማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች አስተያየት መስጫ በኩል አልያም በሌላ መንገድ የሚላኩ የኪነጥበብ ሥራዎች በውድድሩ አይካተቱም ወይም ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ። የተሟላ የተሳትፎ ቅጽ ያላያያዙ የኪነጥበብ ሥራዎች ወይም መረጃ በተሟላ መልኩ ያላቀረቡ የኪነጥበብ ሥራዎች በውድድሩ አይካተቱም ወይም ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ። በሲዲው (CD) ወይም በፍላሽ ዲስኩ (USB) ለውድድር ከሚቀርበው የኪነጥበብ ሥራ ውጪ ሌላ ምንም ዐይነት ይዘት ሊኖር አይገባም። ግልጽ ያልሆነ፣ የማይነበብ ወይም ሌሎች የቴክኒክ ግድፈቶች ያሉበት ፋይል አልያም ከሌሎች ይዘቶች ጋር የሚላኩ የጥበብ ሥራዎች ከውድድር ውጪ የሚደረጉ ሲሆን፣ ለዚህም የኢሰመኮ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል። 

ሽልማቶች

ደረጃየፎቶግራፍ ውድድር አሸናፊዎችየአጫጭር ፊልሞች ውድድር አሸናፊዎች – የጀማሪዎች (5-6 ደቂቃ)የአጫጭር ፊልሞች ውድድር አሸናፊዎች ባለሙያዎች (10-15 ደቂቃ)
አንደኛ 75 ሺህ 100 ሺህ125 ሺህ 
ሁለተኛ 50 ሺህ 75 ሺህ100 ሺህ 
ሦስተኛ25 ሺህ 50 ሺህ75 ሺህ